Former Ethiopian Armed Force Worldwide
አስታዋሽ ያጣው ሰራዊትና መና የቀረው መስዋእትነት!!!
በአንድ ሃገር ውስጥ የመከላከያ ሰራዊት እንዲመሰረት ሲታሰብ አላማው አድርጎ የሚነሳው በዋናነት የሃገሪቱን የየብስ፣የባህርና የአየር ክልል ከጠላት ጥቃት ለመከላከልና የሃገሪቱን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ነው።
በርግጥ ቀደም ባለው ጊዜ የ 1ኛውንና የ 2ኛውን የአለም ጦርነት የሰራዊት አደረጃጀት ታሪክ መለስ ብለን ብናስብ የተለያዩ የአለም አገሮች የአለምን የሃይል ሚዛን ሊያዛባ በቻለ መልኩ ግዙፍ የመሳሪያና የሰራዊት ሃይል የገነቡት የራሳቸውን አገር ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን የሌሎችን ሉአላዊ ክልል በመጣስ ሃገርቱንና ህዝቧን በቅኝ ግዛታቸው ስር አውለው ርካሽ የሰው ጉልበትና የተፈጥሮ ሃብታቸውን ለመዝረፍ ነበር።
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ግን የሃገሩን ሉአላዊነትና አንድነት የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር አንድም ጊዜ የሌላውን ግዛት የደፈረበት ሊጠቀስ የሚችል ታሪክ የለም፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሌሎች ሃገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብቷል ከተባለ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥላ ስር ደቡብ ኮሪያና ኮንጎ ዘምቶ በክብር የተመለሰበት ታሪክ ብቻ ነው።
ዛሬ ወያኔ ሽብርተኝነትን መዋጋት በሚል ሰበብ በሶማልያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ የሚያንቦጫርቀውንና ሰራዊቱን አላስፈላጊ መስዋእትነት የሚያስፈልገውን ሳንጨምር በሩዋንዳ፣ በምእራብ ሱዳን ዳርፎርና በደቡብ ሱዳን አቢዬ የተሰማራው የወያኔ ሰራዊትም ቢሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥላ ስር ነው።
የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንኳንስ በሌሎች አገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሊገባና ወረራ ሊፈጽም ቀርቶ ለራሱም ያለምንም እረፍት ከሚስቱ ከልጆቹና ከዘመዶቹ ተለይቶ ደርቅ ኮቸሮ ቆርጥሞ፣ድንጋይ ተንተርሶ፣ደሙን አፍሦ፣ አጥንቱን ከስክሶ ህይወቱን ገብሮ ከ30 አመት በላይ ከውስጥና ከውጪ የሃገሪቱ ጠላቶች ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ሲተናነቅ የኖረና በመጨረሻም የሃይል ሚዛኑ ወደተባበሩት የኢትዮጵያ ጠላቶች ሲያጋድል በግፍ የተበተነ ሰራዊት ነው። ወያኔ ሃገር ከማስገንጠልና የባህር በር ከማሳጣት ባሻገር በሰራዊቱ ላይ የፈጸመው ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል አንድም ቀን ከወያኔና ከሻአቢያ ጋር ተዋግተው የማያውቁና ከሶማልያ ጋር በተደረገው ሃገር የማዳን ጦርነት አካላቸው ጎድሎ በጀግኖች አምባ ተሰብስበው መንግስት እየረዳቸው የነበሩትን የሃገር ባለውለታዎች እያዋረደ ከአምባው ማባረሩና በህጻናት አምባ የነበሩትን ወላጆቻቸውን በጦርነት ያጡ ህጻናትን ከአምባው አባሮ ለልመናና ለጎዳና ተዳዳሪነት የዳረገበትን ሁኔታ ሳስበው ነገ የወያኔም ጀንበር ስትጠልቅ ሊጠቅ ስለሚገባው ጥያቄ ዛሬ ላይ ሁኜ ሳስብ የበቀል ስሜቴን ያንረዋ።
በነዛ መራር 30 የትግል አመታት ውስጥ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት ከጀበሃ፤ከሻቢያ ፤ከወያኔ፤ ከኢሃፓ፣ ከመኢሶን፣ ከኢዲህና ከኦነግ ጋር የተደረገው ትንቅንቅ ምንም እንኳን ደርግን የጎዱ መስሏቸው ከሶማልያና ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር የተሰለፉ ቢሆንም የተደረገው መገዳደል ለኢትዮጵያ የተሻለ የፖለቲካ አማራጭ ያለኝ እኔ ነኝ በማለት ባለመደማመጥ የመጣ ጥፋት ነው ብለን ብናምን እንኳ ወያኔና ሻአቢያ ይዘውት ከተነሱት የመገንጠል አላማና ከጀርባቸው ካሰለፉት የጥፋት ሃይል አንጻር በተለየ መልኩ እንድናያቸው ያስገድደናል።
ሻአቢያና ወያኔ ገና ከመነሻው ይዘውት የተነሱት አላማ ኤርትራንና ትግራይን መገንጠል ፣ኢትዮጵያን የባህር በር ማሳጣት፣ ታላቋን የትግራይ ትግሪኚ መንግስት ማቋቋም ነው፡ ይህንን አላማቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ ከኢራን፣ከኢራቅ፣ ከሊቢያ፣ ከሱዳንና ከሳውድ አርቢያ በብዙ ሚሊዮን ይሚቆጠር የመሳሪያና የገንዘብ እርዳታ ብቻ ሳይሆን የዲፕሎማሲ ድጋፍም በከፍተኛ ደረጃ ነበራቸው፣ ይህ ብቻ ሳይሆን የመሳሪያ እርዳታ ለማግኝት ሲሉ ከሶማሊያ ወታደሮች ጎን ተሰልፈው የኢትዮጵያን ሰራዊት ወግተዋል።
እንግዲህ የቀድሞው የኢዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አብዮታዊት እናት ሃገር ወይንም ሞት! በማለት 17ቱንም አመት ሙሉ የሞትና ሽረት ትግል ሲያደርግ የቆየው ከነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ሀገሮችና ከጀርባቸው ያሉት ምእራባውያን መንግስታት ከወከሏቸው የእናት ጡት ነካሽ ከሃዲ ወንበዴዎች ( ሻአቢያና ወያኔ) ጋር ነበር ማለት ነው።
ከቤተመንግስት ጀምሮ እስከ ዋናው የጦር ግንባር በዘረጉት ኔትወርክ የውስጥ አርበኞች የሰራዊቱን የውጊያ ሚስጥሮች አስቀድመው ለጠላት እንዲደርስ በማድረግ ፣ ጥይት ሲጠየቅ ቀለብ፣ ቀለብ ሲጠየቅ ጥይት በመላክ ፣ ሰራዊቱን እርስበርሱ ሳይተዋወቅ እንዲዋጋ በማድረግ፣ በስህተት ነው እያሉ የወገንን ሰራዊት በወገን አውሮፕላን በማስደብደብ በሰራዊቱ ህይወትና የውጊያ ሞራል ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማደረስ ፣ ሰራዊቱ ለበተሰቡ የሚልከውን ተቆራጭ ገንዘብ በወቅቱ ባለማድረስና በመብላት ድርብ ግፍና በደል በሚፈጽሙ ፣አገር ለማስገንጠልና የበህር በር ለማስዘጋት ከጠላት ጎራ በሚሰለፉ እንደ ጄኔራል አብዱላሂ ኡመርና ጄኔራን ጥላሁን ክፍሌ አይነት ከሃዲ መሪዎች ባሉበት ሁኔታ ነው 30 አመት ሙሉ በጽናት ላቡን፣ ደሙን፣ አካልና ህይወቱን ሲገብር የኖረው።
ሰራዊቱ አብዮታዊት እናት ሃገር ወይንም ሞት!! አለ እንጂ አንድም ቀን መንግስቱ ሃይለማሪያም ወይንም ሞት!! ብሎ አያውቅም፤ ይህን በመሰለ ሁኔታ ውስጥ ነው እንግዲህ በግፍ የተበተነውን ሰራዊት የደርግ ጦር፣ የመንግስቱ ወታደር በማለት ሊያሳንሱት ይሚፈልጉት፤
እናም ዛሬ ላይ ሁኜ ሳስበው መጠየቅ የሚገባው ቀዳሚ ጥያቄ ያ ግዙፍ ሰራዊት ለምን ተሸነፈ? ተብሎ ሳይሆን በዚያ ሁሉ ጠላት መሃል በውስጥም በውጪም ተወጥሮ ፣የሶማሊያን ወረራ በጀግንነት መልሶ የሰሜንና የመሃል አገሩን ችግር እየተጋፈጠ ሳይበታተን በትእግስትና በጽናት እንዴት 30 አመት ሙሉ ቆየ ተብሎ ነው መጠየቅ ያለበት ፤ ያንን ስናደርግ ነው የዚያን ሰራዊት ማንነትና ምንነት የምንረዳው። እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ። በ. ገ 25/01/2015

Comments
Post a Comment