//ጣይቱ ሆቴል1898 ዓ/ም //
የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሆቴል ሲሆን የተሰራውም ለንግድ ተብሎ ሳይሆን ሀገራዊ ራዕይን ለማሳካት ታስቦ ንብረትነቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲሆን በበላይ ሁኖ የሚቆጣጠረው ደግሞ ሀገሪቱን ተረክቦ በኃላፊነት የሚመራው መንግሥት ነበር ።
የጣይቱ ሆቴል የእቴጌዋ ቤተሰቦች ከጎንደር መጥተው እንውረስ አላሉም ቢሉም አይሆንም እንዳሁኖቹ ጠባብ ቡድኖች በቤተ ሰብ አያምኑም ነበር ።
ወደ አድዋም ሲዘምቱ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀ አውሮፓዊ ጦር ለመግጠም ሙሉ ለሙሉ እናሸንፋለን ብለው አልነበረም ነፃነት ወይም ሞት ብለው እንጅ እንደነ መምህር ገብረ ኪዳን ያሉት የሀሰት ፀሐፊ ቢሆን ኑሮማ ከአንኮበር ቤተ መንግሥት ሁነው እንደነ ደጃች ጉግሳ አርዓያ ኤርትራ ድረስ ሂደው አበባ ይዘው ጣሊያንን ይቀበሉ ነበር ።
ታሪክ ሁሌም ይኖራል ።
ይህ ለዘመናት የሕዝብ ንብረት የሆነው የቴጌ ጣይቱ ሆቴል እንዳለመታደል ሁኖ በሕውሓት ዘመን ደረሰና ምርጥ ምርጡ ለራሴ በሚለው ፖሊሲ የአንድ መንደር ሰዎች ተሰባስበው የሀገርን ቅርስ ሳይቀር እሰከመሸጥ ተደረሰና ሻጩ የፕራቤታይዜሽን ኃላፊ የሆነው የሰዬ አብርሃ ወንድም አሰፋ አብርሃ ሻጭ ገዥው ደግሞ የባለሥልጣኑ የሚስት ወንድም ፍፁም ዘአብ ሁሉ የአንድ ጎጥ ሰዎች በዚህ መልኩ ለአቶ ፍፁም ዘአብ የሀገር ቅር ስ የሕዝብ ሀብት ለግል ንብረት እንዲሆን ተሸጠ ተባለ ። ይህ ብቻ አደለም ለዚህ ግለሰብ የሕዝብ ሀብት የተሸጠ የጉለሌ የሣሙና ፋብሪካ ፣ የሐረር ማተሚያ ቤትም ጭምር ነበር መቸም በልተው አይጠግቡ ።
እኛ በተለምዶ ጣይቱ ሆቴል ሥንልለካስ ባለቤቱ አቶ ፍፁም ዘአብ ናቸው ። ምን ይባላል ?
ሕውሓት ሁሉም በእጁ፣ ሁሉም በደጁ እሱ ዳኛ እሱ ፈራጅ ፣ እሱ ከሳሽ ፣ እሱ አሳሪ ፣ እሱ ገዳይ ፣እሱ አዳኝ ።
ሀገራችን እውን አለች? አለች የምንል ተሳስተናል ።
እኔ አገሬን ካጣኋት 23 ዓመታትን አሳልፌ 24ኛው የዠዋለሁ ።
Like ·  · 

Comments