- Get link
- X
- Other Apps
―※ ኢትዮጵያ በወያኔዎች ዓይን ※―
ሕውሓቶች ልክ እንደ ጥብቆአቸው የለኳት ኢትዮጵያ አጥራና ቀጥና እጅግም ኮስምና ነው በነሱ እይታ ።
አዎ እጅግም ኮስምና ፣
ምንም ያልነበራት ፣
ምስኪን ኢትዮጵያ ፣
የመነሻም የመድረሻም እሴት የሌላት የታሪክ ፣የባሕል ፣የዕምነት የምንም ባለቤት ያልነበራት ።
የተፃፉትም ሆነ ያልተፃፉት አፈ– ታሪክ ሀሰት ከመሆኑም በላይ ፣ የፃፍትን ፣ የተናገሩትን ሁሉ ተጠያቂም ከማድረጉም በላይ የተወሰነውን ሕብረተ ሰብ ነጥሎ በኃላፊነት የሚክስ ፣ ከሱ በፊት የቆየውን ነባራዊ ሁሉ አጥብቆ የሚጠላ የሚያጥላ እርባና ቢስ ዋጋ የሌላቸው እንደሆኑ ነው የሕውሓት ዓይን የሚያውቃቸው ።
አዎ ምስኪን ኢትዮጵያ የመቶ ዓመት ባለ ታሪክ በወያኔ እይታ ።
እንደ ወያኔዎች እይታ ብሶት የወለደው ሕውሓት ባይደርስ ኑሮ ኢትዮጵያ እስካሁን ግብዓተ መሬቷ ተፈፅሞ ለ24ኛ ጊዜ ዝክረ መታሰቢያ እናደርግ ነበር ።
ብሶት የወለደው ሕውሓት መጣና እነሆ ታሪክ አልባዋን ኢትዮጵያን ፣ፍትህና ርትዕ የሰፈነባት ፣የብሔር ብሔረ ሰብ እኩልነት ፣ በዓለም እጅግ ተወዳዳሪ የማይገኝለት እንደ ኢትቪ ዘገባ የዲሞክራሲ መብት በአካፋ የሚዛቅባትን ኢትዮጵያን የፈጠሩባት ።
ሰው በዘሩና በቋንቋ ምንም ተፅዕኖና አድልዎ ሳይደረግባት እንደፈለገ ተንቀሳቅሶ የሚሰራባት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ምሁር በዘሩ ሳይሆን በችሎታው ተወዳድሮ የስራ እድል ያለባታ ያች ምስኪን የነበረች ታናሽ አገር አሁን እንደ ኢትቪ ዘገባ ምድራዊ ገነት ኢትዮጵያ ናት አዎ መታደል ነው የዛሬዋን ኢትዮጵያ ዜጎች ከማንኛውም ዘመን ከማንኛው ሥርዓት በዜግነታቸው በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩባት ሀገር የፈጠሩልን ሕውሓት – ኢህአዴግ በኢቲቪ ና በሚዲያ አውታራቸው ብዙ የተዘመረላት ይች ሕውሓት ሰራሿ የማን ናት ማንስ አያት ማንስ ዳሰሳት። እሰዬው ነው ¡¡¡
አወ !!!!
ኢተዮጵያዊ መሆን በአሁኑ ዘመን በዓለም ፊት ቀና ብለን እጅግም ተከብረን የምንታይበት ዘመን በተለይ በአረብ ሀገራት የሚሰጠን ክብር ለውሾች ከሚሰጣቸው ባላነሰ መልኩ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም ለዚህ ያበቃንን ፀሐዩን መንግሥት “ ሳናመሰግን “ አናልፍም ። ።
አወ !!!!
ብሶት የወለደው የኢትዮጵያ መንግሥት በፈጠረላቸው የዲሞክራሲ መንገድ ተጠቅመው ሁሉም ዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮአቸው እየበለፀገና እየዳበረ በመምጣቱ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ በመሹለክ ለሽርሽር ከሀገር እያመለጡ ይገኛሉ ። ይህም የፀሐዩ መንግሥት አስተዋፅኦ መሆኑን ማንም ሊዘነጋው አይገባም ።
ዜግነት በኢትዮጵ ጠባብነት በመሆኑ እምብዛም ዋጋ አይኖረውም ። በፀሐዩና ብሶት በወለደው በሕውሓት ኢህአዴግ መንግሥት ዜግነት በብሔር ወየም በዘር መተካቱ አዋጭነቱ ከፍተኛ ነው ተብሏል።
ለምን ቢባል ዜግነት ለአድልዎ በር ይከፍታል ትምክህትን ያስከትላል።
አንድ ዜጋ ነኝ ብሎ የሚኩራራ ከሆነ ዜግነት የሌላቸውን እንደነ ቻይና ያሉትን ዘመናዊ የአፍሪካ ኮሎኒያሊስቶች በኢትዮጵያ እጅጉን የሚጎዳ በመሆኑ ታሳቢ ተደርጎ የውጭ ዜጎችን ያለገደብ ተጠቃሚ ያደርጋል ።
አወ !!!!!!!
ባዕዳን በኢትዮጵያ ከማንኛውም ዓለም ፣ ከማንኛውም አህጉር ፣ በበለጠ መብት የተከበረላቸው ሲሆን የጠየቁትን ያገኛሉ የፈለጉትን ይሰራሉ እሰዬው ያስብላል ።
ይህ ነው በባዕዳን የተመሰከረላት ምቹ ሀገረ ኢትዮጵያን ያገኘናት ።
ዜጎቿ በግልባጩ ወደባዕድ ሀገር ለቢዝነስ በብዛት ሲወጡ መንግሥታቸው የፈጠረላቸውን አጋጣሚ በተራቸው ከሳውዲዎች ጥሩ አቀባበልና ከበሬታ እየተቸራቸው መሆኑን በየቀኑ የሚወጡ ዘገባዎች የሳውዲን ብሔራዊ ገፅታ ግንባታን የኢትዮጵያውያን አስተዋፅኦ በማድረጋቸው እጅጉን የሚያኮራ ከመሆኑም ባሻገር ለዚህ ባለውለታ መንግሥታችን ጋር ወደፊት እንድንል ያደርጋል ብለዋል።
- Get link
- X
- Other Apps

Comments
Post a Comment