The Meeting is held about the on going genocide in Ethiopia by TPLF:
አቶ ጌታቸውረዳ በትግራይ (አክሱም) የተወለዱ ሲሆኑ ብዙ ጊዜ የወያኔን ድርጊት በተጨባጭ ማስረጃዎች በማጋለጥ ይታወቃሉ። እርሣቸውም
ለተሰብሳቢዎች እንዳብራሩት፣ ሕዝባዊት ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሥልጣን በመሣሪያ ኃይል ከተቆጣጠረ በኋላ፣ በሕዝባችን ላይ በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለጆሮ የሚከብዱ፣ ለዓይን የሚቀፉ፣ እንዲሁም በአገራችን ሉዐላዊ ክብር እና በዐማራው ነገድ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው አስነዋሪ ወንጀሎች
መፈፀማቸውን አስረድተዋል። አቶ ጌታቸው፣ ከሁሉም በላይ በዐማራው ነገድ ላይ
ያነጣጠረው የወያኔ ጥቃት በምንም መለኪያ ከሌሎች ነገዶች ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋርሊወዳደር የማይችል አሰቃቂና ዘግናኝ እንደሆነአስምረውበታል። ዐማራው ለዘመናት ከኖረባቸውአካባቢዎች በኃይል«ውጣ» እየተባለ ከነቤተሰቦቹሲባረር፥ ኦሮሞው፣ ትግሬው፣ አደሬው፣ሶማሌው፣ አፋሩ፣ ጋምቤላው፣ ወላይታው፣ወዘተርፈ... አለመባረሩን በንፅፅር አሳይተዋል።በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ዐማራው ከነነፍሱ ወደ
ገደል ተገፍትሮ መጣሉንና ለከፍተኛ አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ መዳረጉን በማውሳት፣ እጅግዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋ እንደተካሄደበትአስረድተዋል። ሌሎች ነገዶች በዐማራው ዓይነትእና መጠን ጭፍጨፋ እንዳልተካሄደባቸው በማስገንዘብ፤«ዐማራው ለምን ለብቻው ጥቃቱ አንዲነገርለት ተፈለገ?»ብለው ለሚጠይቁ ዜጎች፣ እየደረሰበት ያለው የዘር ጥቃት የከፋና የመረረ
በመሆኑ፣ ዘሩን ከፈጽሞ ጥፋት ለመታደግ ስለእርሱ መጮህ ተገቢ እንደሆነ አስረድተዋል። አቶ ጌታቸው አያይዘውም የዐማራው
ጠላቶች በርካታ መሆናቸውን በማስገንዘብ፣ እንዲያውም እርሳቸውም በስብሰባው ተገኝተው የዐማራውን ብሶት እንዳይናገሩ በጽሑፍ እና በስልክ መልእክቶች አማካይነት የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎች የደረሷቸው መሆኑን ገልጸዋል። ይህንም ያደረጉ ግለሰቦች የዐማራውን ልዩ ጥቃት መረዳት የተሳናቸው ግብዞች መሆናቸውን እንደሚያምኑ ገልጸዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ አያይዘውም፣ እነኚህ ግለሰቦች ያልተረዱት ነገር፣ ዐማራው ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተለይቶ
በሻዕቢያ፣ በወያኔ፣ በኦነግ፣ «ዓረባዊ ነኝ»በሚለው ኦብነግ እና በተቃዋሚውም ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ዐማራ ኤሊቶች አማካይነት በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የአካል እና የሥነ ልቦና ስብራት መድረሱን ያለመገንዘባቸውን ነው። የእነዚህ ቡድኖች እና ልሂቃን በጻፏቸው እና ባሠራጯቸው የዐማራ ማጥላያ መጽሐፍት
ዐማራውን እንደቀጠቀጡትም አጋልጠዋል። ለምሣሌም በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተጻፈውን «የአማራ ሕዝብ ትግል ከየት ወዴት»የሚሠኘውን መጽሐፍ በአስረጅነት አቅርበዋል።ዐማራው በጥይት መረሸኑን፣ እርጉዝ እናቶች እና
እህቶች ከነሕይዎታቸው ወደ ገድል መወርወራቸውን፣ ከሚኖሩበት አካባቢ በጉልበት ተገፍተው ንብረታቸው ሳይዙ እና ከቤተሰቦቻቸው
እየተነጠሉ፤ አንዳንዶቹ ከመቅጽበት፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በ፳፬ ቢበዛም በ፵፰ ሰዓት የጊዜ ገደብ እየተጣለባቸው አንዲባረሩ መደረጉን በቁጭት አስረድተዋል።አቶ ጌታቸው በዚህ ማብራሪያቸው፣ በጥቂት ዓመታት ልዩነት የሌሎቹ ጎሳዎች የሕዝብ ቁጥር ሲጨምር የዐማራው ነገድ ግን በ፪ ሚሊዮን
ከምድረገጽ መጥፋቱ በወያኔም ስታትስቲክስ ምሥሪያ ቤት ጭምር ታምኖበት በፓርላማ ተብየው በሪፖርት መገለጹን አብራርተዋል። አያያይዘውም፣ በወጣት እናቶች እና በአዛውንቶች ክብር ላይ ጥቃት መፈጸሙን፣«ዓይነ ስውራን» ወንዶች አዛውንት ብልታቸው፣ እናቶች ደግሞ
ጡታቸው በቢላዋ መቆረጡን፣ ሕፃናት
በትምህርት ገበታ ላይ አንዳሉ የየክፍሎቻቸውን
መዝጊያዎች በመቆለፍ ከነነፍሳቸው በእሳት
ተቃጠለውና ተሰቃይተው እንዲሞቱ መደረጉን፣
እናቶች አንዳይወልዱ ማኅጸናቸው አንዲደርቅ
መርዝ መወጋታቸውን ከመግለጻቸውም
በተጨማሪ፣ አሁንም ጥቃቱ አለማባራቱን
አስረድተዋል።
ግብዦቹ፣ ይህንን ጥቃት አታጋልጡ
እንደሚሉ ጠቅሰው፣ ይህ ጉባኤ ስለ ዐማራ ጥቃት
እና ውርደት ስቃይና መከራ ለሕብረተሰብ መንገር
ፀረ ኢትዮጵያዊነት አለመሆኑን እና የዐማራው
ሕብረተሰብ ጥቃት ተሸፍኖ እንዲቀጥል
በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አስተዋጽዖ የሚያደርጉ
ወገኖች እንዳሉም አስረድተዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ማብራሪያቸውን
በማዳበር፣ ኢትዮጵያዊያን አገር እና ትውልድ
የማዳን የዜግነት ግዳታቸውን አንዲወጡ
ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ከሁሉም በላይ ከዐማራ
ማኅብረሰብ የተወለዱ ውጭ አገር እና ውስጥ
አገር የሚኖሩ የሕግ ጠበቆች በየድረገጹ
የሚያቀርቧቸው ሳምንታዊ/ወርኃዊ
«የፖለቲካ ጅላጅል ትንተናቸውን»
አቁመው የወላጆቻቸውን
እና የእህቶቻቸውን የድረሱልን ጥሪ ተቀብለው
ወንጀለኞቹን ወደ ሕግ አደባባይ የማቅረብ
ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ጌታቸው ያለንበት ዘመን የክህደት ዘመን
መሆኑን ጠቅሰው፣ በመንደላቀቅ እና በምቾት ኑሮ
በውጭም በአገር ውስጥም ጆሮውን ደፍኖ ሰምቶ
አንዳልሰማ ያጠረመመው የዐማራው ልሂቅም ሆነ
በሕብረ-ብሔር የፖለቲካ ድርጅቶች ጭንብል
ተጀቡኖ ከሻቢያ ቡድን ጋር ትከሻ ለትከሻ እየተሻሸ
ያለው ዐማራ የገዛ ወገኖቹን እንደጎዳ ኮንነዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ዐማራን እያጠቃ ካለው
የወያኔ ቡድን እና መሪያቸው ጋር በመተባባር፣
የዐማራን ተወላጆች በመጽሐፎቻቸው እና
በሕዝባዊ ስብሰባ ንግግሮቻቸው የዘለፉ፣
እንዲሁም ትውልዱን የከዱት
«የንጉሥ ተፈሪ የልጅ ልጆች ነን»
የሚሉ ውጭ አገር እና በአገር
ውስጥ የሚኖሩ መሣፍንት እና ልዑላን
እንደሆኑ አስረድተዋል ።
ስለ አማራው ጥቃት መነጋጋር ማለት ስለ
ኢትዮጵያ ጥቃት መነጋጋር ማለት እንደሆነ
የገለጹት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ስለ ዐማራው
መጠቃትና ጥቃቱን እንዴት እናቁመው ብሎ
መነጋገር «እንዴት ጐሰኝነት ሊያስብል ይችላል?»
በማለት ጥያቄ አቅርበዋል [1]።
ሙሉውን ጽሑፋቸውን በሚከተለው አድራሻ
ማግኘት ይቻላል፦ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን
ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)፣ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ስቴት-ሳንሆዜ ከተ
«የዐማራውን ሕዝብ በፀሎት እና
በለቅሶ ብቻ ማዳን አይቻልም»
አቶ ከተማ ደሜ
በስቶክሆልሙ ስብሰባ ሌላው ተናጋሪ
የነበሩት አቶ ከተማ ደሜ ነበሩ። አቶ ከተማ
ትውልዳቸው እና ዕድገታቸው ጎሬ ከተማ፣
ኢሉባቦር ሲሆን፣ አባታቸው ከጅማ እናታቸው
ደግሞ ከወለጋ የሆኑ፣ በወያኔ ቋንቋ
«ኦሮሞ» ናቸው። ነገር ግን ዳኛ ከተማ ደሜ ከኦሮሞ
ብሔረተኝነት ይልቅ በኢትዮጵያዊነት ጽኑ
እምነት ያላቸው እና ነገን አሻግረው ማየት
የሚችሉ ኩሩ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው
ለስብሰባው ተካፋዮች ጠንካራ መልዕክት
ለማስተላለፍ በቅተዋል። አቶ ከተማ በስዊድን
ሀገር በሙያቸው በፍርድ ቤት ውስጥ ከ፲፫
ዓመት በላይ በማገልገል ላይ ያሉ ናቸው። አቶ
ከተማ በንግግራቸው ”ዐማራው ከተደራጀ እና
ከጠነከረ ራሱንም ሆነ ሌላውንም ነፃ
ለማውጣት ይችላል፣ አሁን ግን ፳፪ ዓመት
ሙሉ ተኝቷል። ዐማራው መብቱን ለማስጠበቅ
ተደራጅቶ በአንድነት መቆም አለበት። ራስን
ለመከላከል እና ራስን ለመጠበቅ በአንድነት
መነሣትን እንኳን ሰው፣ አውሬም ያደርገዋል።”
በማለት መልዕክታቸውን በፓልቶክ የመገናኛ
ዘዴ አስተላልፈዋል። አቶ ከተማ በፓልቶክ
ያስተላለፉትን መልዕክት ለማዳመጥ፣
ዳኛ ከተማ ደሜ ንግግራቸውን የጀመሩት
የወያኔዎችን ዐማራውን የማጥፋት ዓላማ፣
ከሒትለር እና ከሞሶሎኒ ፍልስፍናዎች እና
ድርጊቶች ጋር በማነፃፀር ነበር። እንዲሁም ስለ
ኦነግ ሲናገሩ፦ ሻቢያ እና ወያኔ የኢትዮጵያን
ጦር ለመውጋት ሻቢያ ኦነግን እንደፈጠረ
ሆኖም «ኦነግ በአጼ ኃይለሥላሤ ዘመን
ተፈጠረ» የሚባለውም ውሸት ከመሆን አልፎ
እርሣቸው ግብፅ በነበሩበት ጊዜ በተጨማሪ
ግብጻውያን ኦነግን ለመፍጠር እንዴት
ይሯሯጡ እንደነበር የዓይን ምስክርነታቸውን
ገልጸዋል። በመቀጠልም ይህ የሻቢያ እና የወያኔ
ዕቅዳቸው ተሣክቶላቸው እነርሱን ተሸክሞ
አዲስ አበባ ያስገባቸው ኦነግ መሆኑን
አስረድተዋል። ሻቢያ እና ወያኔ ቁጥር ፩ እና ፪
ዕቅዶቻቸው ተሣክተውላቸው (ኦነግን
መፍጠርና በኦነግ ትክሻ አዲስ አበባ መግባት)
ቁጥር ፫ የሆነውን ተከታዩን ዕቅዳቸውን
በማስፈፀም ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ሦሥተኛው ዕቅዳቸው ዐማራን በማጥፋት
ኢትዮጵያን ከዓለም ካርታ መፋቅ እንደሆነ
አመልክተዋል። ለዚህ ዕቅድ አፈፃፀም ወያኔዎች
የሚከተሉት ሥልት ዐማራውን ሕዝብ
በማጥፋት እንዳይወቀሱ እና እንዳይጠየቁ፣
«ዐማራውን በኦሮሞዋች ማስመታት ነው»
ብለዋል። እንደ አቶ ከተማ አተያይ
«ተማሩም አልተማሩም፣ ብዙ ሰዎች ይህን የወያኔ ዓላማ
የተረዱት አይመስልም» ሲሉ ወቅሰዋል።
በንግግራቸው፦«ወያኔዎች ኢትዮጵያን
ለማጥፋት እንጂ ለማልማት እና ለማስተዳደር
እንዳልመጡ እየታወቀ ሆኖም ብዙ ሰዎች
ወያኔን “የኢትዮጵያ መንግሥት” ብለው
ይጠሩታል። ጥያቄው መሆን ያለበት
”የኢትዮጵያ ሕዝብ እነዚህን ሰዎች ምን ያህል
አውቋቸዋል?” ነው። ችግራችን ቁርስ የበላነውን
ማታ እንረሣለን፣ የኛ ችግር እነርሱ ነገ
ተለውጠው እንደ እኛ ኢትዮጵያዊ ይሆናሉ
የሚል እምነት አለን። እነርሱ በዚህ
አስተሳሰባችን ይስቁብናል፣ ”ኢትዮጵያዊ ነን”
የምንለውን እንደሙሉ ሰው አያዩንም።
ምክንያቱም እነርሱ ሲጠሉን እኛ ግን
“ልጆቻችን፣ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን
ናቸው” ስለምንል ነው። እነርሱ ግን እንደ እኛ
“ወንድሞቻችን ናችሁ” ብለው ተናግረው
አያውቁም። መለስ ዜናዊ በቢቢሲ እና
በአልጀዚራ ቃለ መጠየቅ ሲሰጥ፣ “እነርሱ”
እያለ ራሱን ከኢትዮጵያዊነት አግልሎ ነው።
“እነርሱ ዲሞክራሲ አይገባቸውም፣ አይረዱም፣
እነርሱን ማስተዳደር የሚቻለው እኛ በያዝነው
መንገድ ብቻ ነው” እያለ ነው። ታዲያ እኛ
የሚጠሉንን ለምንድን ነው መጥላት
ያልቻልነው? ችግራችን የሆድ፣ የሞራል ኪሣራ፣
የመማር ወይስ ያለመማር ነው?» በማለት
በተሰብሳቢዎች ኅሊና ውስጥ ሊብላሉ
የሚገባቸውን መሠረታዊ ጥያቄዎች ጭረዋል።
ስለ ዘመኑ ባንዳዎች ለታዳሚው
በአቀረቧቸው ጥያቄዎች፦
«በጣሊያን ጊዜ ለጣሊያን እንቁላል ያቀብሉትን ሁሉ
“ባንዳ” ብለን እንጠራቸው ነበር፣ ዛሬ ለወያኔ
የሚያገለግሉትን ምን ብለን እንጥራቸው?
ወያኔዎች “ዐማራን ከምድረ ገጽ እናጠፋለን”
ብለዋል፣ ነገር ግን ዐማሮች ዛሬ ከወያኔ ጋር
ይነግዳሉ፣ ለምንድን ነው? ነገ ይገድለኛል
አይሉም? ይህን ማወቅ ይቸግራል? ከባንዳ ጋር
መሥራት ባንዳ አያሰኝም ወይ?» በማለት
ለውይይቱ ደርዝ ሰጥተውታል።
ቀጥለውም፦«ሰው ኦነግን የኦሮሞ
ድርጅት አድርጎ ይመለከተዋል። እኔ ግን የወያኔ
ካድሬዎች ናቸው ብዬ ነው የምጠራቸው።
የወያኔ ዋናው ተልኮው ኢትዮጵያን ማጥፋት
ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ ከጠፋች መጀመሪያ
እርስ በራሱ የሚዋጋው ኦሮሞው ነው።
የወለጋው ኦሮሞ፣ ከሐረሩ፣ የሐረሩ ኦሮሞ
ከወሎም፣ ወዘተርፈ ከሌላው በተለዬ መልኩ
ምንድን ነው አንድ የሚያደርገው? በዕምነትም
የተለያዩ ከመሆን አልፎ እስላሙ ወገን የገዳን
ስርአት ጨርሶ አይቀበልም፣ ከዚህ ተጨማሪ
ከዐማራው ጋር እንዲጋጩ ተሰብከዋል፤» ሲሉ
የፓኪስታንን፣ የባንግላዲሽን እና የህንድን
መገነጣጠል በምሣሌነት አቅርበዋል።
በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት
«ለምንድን ነው ከወያኔ በርበሬ የምንገዛው?
ጤፍ የምንገዛው? ከወያኔ ጋር የምንነግደው?
ወያኔ እኛን እንዲገድል መሣሪያ የምናቀብለው
እኛው ራሣችን ነን። ይህ ራስን ማጥፋት
አይደለም ወይ? ወያኔን ሥልጣን ላይ ያቆየው
የእኛ ድክመት ነው። ሆድ አምላኩና እንቁላል
አቅራቢ የሆኑ በመካከላችን አሉ። በወያኔ ላይ
ማዕቀብ ማድረግ ያስፈልጋል። መረጃዎችን
መሰብሰብና ወያኔን ለፍርድ ማቅረብ
ያስፈልጋል። ዐማራን ለማዳን በተግባር
መሥራት ያስፈልጋል። የዐማራ መኖር
የኢትዮጵያ መኖር ነው። የዐማራ ችግር
የኢትዮጵያ ችግር ነው። የዐማራ ስቃይ
የኢትዮጵያ ሥቃይ ነው። ዐማራን በጸሎት እና
በለቅሶ ብቻ ማዳን አይቻልም። እነርሱ
[ወያኔዎች] ከዓላማቸው በምንም አይነት
አይመለሱም። ከሥልጣን ከወረዱ ደግሞ በዘር
ማጥፋት ወንጀል እንደሚጠየቁ ያውቃሉ።»
በማለት ለስብሰባው ተሣታፊዎች ምን ማድረግ
እንደሚያስፈልግ በአፅንዖት አሣስበዋል።

Comments