ኧረ ስንቱን ላስታውሰው ?
<iframe width="560" height="315" src="https://www.youtube.com/embed/uXvmx1x-Go8" frameborder="0" allowfullscreen></iframe>
<iframe width="560" height="315" src="https://www.youtube.com/embed/uXvmx1x-Go8" frameborder="0" allowfullscreen></iframe>
የሰው ልጅ በምድር ተሽከርካሪ በሰማይም በራሪ በባለብዙ ፎቅ ቤትኗሪ መብላትም መጠጣትም ደስታ ይፈጥርልኛል የሚለኝ ሰው ካለ ሌላ መረጃ ማቅረብ አልችልም ።
ነገር ግን ና በኔ ሁነህ እየው እላለሁ።
እንደኔ እንደ እኔ ሁሉንም አጥቻለሁ ።
መጥፎ ዕድል እንደ እኔ በዓለም የከሰረ የለም ።
የልጅነት ዕድሜየን ያሳለፍኩት እንዲህ ነበር እኔም በዚህ መልኩ ይህን ዓይነቱን ጋብቻ አልፌበታለሁ ለአቅመ አዳም አልደረስነም ነበር ባለቤቴም ለጋ እንቡጥ ፅጌ ረዳ መሳይ የ12 ዓመት ዕድሜም ነበረች በርግጥ በዚህ ላይ የምናየው ለፊልም ሲባል የተሰራ በመሆኑ ለማሳያ ነው እውነተኛውን ባህል አንተም በውስጡ ራስክን ሁነህ ለዓመታት የቆህበት ሲሆን የበለጠ ስሜት ይከትሀል ።
እኔ ብዙ ነገርን አይቻለሁ ነገር ግን ሁሉንም አጥቻለሁ
በመንፈሳዊ ት/ ቤት በ6 ዓመት ጀመርኩ
በየኔታ ዕጅም ተገርፌአለሁ " ረ" በዚች ፊደል ሥም በትክክል ለመጥራት ጀሮዬ እስኪቆስል ተገርፌ አለሁ ።
ከ13 ዓመት በላይ በዚያው ቆይቻለሁ ፣ በዘመናዊው ት/ ቤት እንዲሁ በከረፍለፀ ከ1— 3 ባሉ ደረጃዎች የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃን አጠናቅቄ በትምህርት ለመግፋት የነበረኝ ምኞት በሕዝባዊ ወያነ ሀርነት ሀገርን የመቆጣጠር አጋጣሚ በትምህርት ሳልገፋ ስለሀገር ማሰብና ማውጠንጠን ውስጥ ተጠመድኩ ይህም በምኖርባት የገጠሯ መንደሬ እስከ አካባቢየ ከተማ በወያነ የኮር አባላት የሀሳብ ልዩነቴ ታውቆ ከአብሮ አደግ የትምህርት ቤት ባለንጀሮቸ የማግለሉ ነገር ቀጠለ ያኔ የሕውሓትከሁሉም የሚከፋው ከማሰሩ ከመግደሉም ከማፈኑ በፊት በመጀመሪያ የሚጥልብህ ጫና ቤተ ሰቦችህም ጭምር እንዲያገሉህ ማድረግ ሥለሆነ መገለል በጣም ከባድ ጭቆና አንተን ተወልደህ ባደግህባት መንደር አፈር ፈጭተህ ውኃ ተራጭተህ ከልጅነት ባለንጀሮህ ሲነጥል በመንደርህ ባይተዋር ስትደረግ ከሞት ከእስር ከግርፋትም በላይ የሕሊና ቁስል ያድርብሀል ሆደ ባሻም ያደርግሀል በሀገርህ ሁነህ የወደፊት ሕልምህ ሁሉ ከዓይንህ ላይ እንደጉም ተኖ ይጠፋል በኔ ላይ የደረሰው ይህው ነው።
አንተ በሀገርህ ብዙም ሳትሰራ በለጋ እድሜህ መንግሥትህ ነኝ የሚልህ በጧቱ በዚህ መልኩ መብትህን ሲነሳህ ምን ትላለህ ?
መብት ብቻም አደለም የሕይወት ዋስትናህ ፈተና ላይ ይወድቃል
ለሁለ ዓመት ያክል በዚህ ሰቀቀን ቆይቻለሁ በምንትኖርበት አካባቢ የፀሀይ ብርሃን ከለለ ለመንቀሳቀስ ትፈራለህ ።
ገዳይህን አታውቅም ሁሉም የሕውሓት ደጋፊ የሆነ ሁሉ አንተን የሚያይህ እንደ ሀገር ከሀዲ ጠላት ነው የሚቆጥርህ የሚነገራቸውም በአለቆቻቸው ይህው ነበር ።
Comments
Post a Comment