አንተ ማነህ ለምትሉኝ ዘመዶቸ
                                   
                                                        ሥሜ  እሸቱ ካሳ እባላለሁ

በሀገሬ ኢትዮጵያ ከትውልዴ እስከ እድገቴ ያለፍኩበት ትዝታ በህይወት ዘመኔ አብሮኝ የሚኖር ነው እረሳዋለሁ ብልም አልቻልኩም ።
ለኔ ዘመናዊ ከተማ ዘመናዊ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ለኔ ምኔም አይደሉም ።
ሰለጠን የሚሉኝ ዘመናዊ ሰዎች ለኔ ምኔም አይደሉም።
አራዳ ነኝ ማለት ለኔ ምኔም አይደለም ለራሳቸው ለአራዳዎቹ ትቸዋለሁ ።
መፃፍና ማንበብ ከማያውቁ ቤተ ሰብ ከአፈር ገፊዎች ብወለድም ከቤተ ሰብ የተማርኩት የሀገር ፍቅር በደሜ ውስጥ ስለገባ በዘመናዊ ሕክምና ለመፋቅ የማይሞክርም ነው ።
አወ እሴቱ አያቴ ሰዎች ሰብሰብ ሲሉ የቆውንና የቀድሞውን ሀገር ወዳድ ታላላቅ ሰዎችን ታሪክ በአስቂኝ ቀልድ አጅባ ስትጫወት ሁሉም ታዳሚዎች ሲሰሟት ቢውሉ አይጠግቧትም ነበር ።
አሁን ላይ ሁኜ ሳስበው የአያቴን መሞት ሳስበው ለኔ ታላቅ ቤተ መፃህፍት እንደተቃጠለብኝ እቆጥረዋለሁ ።
አሁን ላይ በዚህ የፌስ ቡክ ገፆች ላይ የቆዩትን ታሪክ ከፎቶ ግራፍ ጋር አጣቅሰው ሲለጠፉ የማያቸው ከሴቲቱ አያቴ ስሰማቸው የነበሩትን ነው ።
እሴቷ አያቴ አትፅፍም አታነብም ከጎንደር ያለፈ ሌላ አገር አልተረገጠችም
ግን ለሴቲቱ አያቴ የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር ጋራ ና ሸንተረር እንዲሁም ጉራንጉር አያግዳትም ነበር ።
ስለአድዋ ጦርነት ፣እስከመተማ ጦርነት ከሰገሌ እስከ አንችም ከውጫሌ እስከ ወልወል ከኡጋኔን እስከ ደጉአሌ ከአክሱም እስከ ዛግዌ ዋግሹም ከአንኮበር አፄ ይኩኖ አምላክ እስከ ሚኒሊክ ያለውን ታሪክ ታጫወተው ነበር።
በርግጥ እኔ እንደምገምተው አንድ የቅርብ ዘመድ የምትወደው አብረው የሚኖሩ ነበር ነበር ይህ ዘመዳችን በሰገሌው ጦርነት በአካል የተሳተፈ የንጉሥ ሚካኤልን ልጅ ያገባ ነበረ ከንጉሥ ሚካኤል ወገን ሁኖ የራስ ተፈሪን ጦር ለመመከት አጥብቆ የተዋጋ ስለነበር አፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሥ ሁነው ሲሾሙ ይህን ዘመዳችን በሀገሩ በኢትዮጵያ ምንም መብት እንዳይኖረው መንግስታዊ ሥራ ቀርቶ ሌሎች ሕዝባዊ የሆነ ነገር እንዳይሰራ ከተማ መኖርም ጭምር ታክሎበት በገጠሯ ኢትዮጵያ ብቻ መኖሪያው እንዲሆን በዙፋን ችሎት በንጉሡ ፊርማ ፀድቆ ቀሪ ዘመኑን በትውልድሥፍራው በዛች የገጠር መንደር ይኖር ነበር እኔም በአካል ደርሸ ለማወቅ ችያለሁ።
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርእስከ 1973 ዓ / ም በዛው በገጠሯ ቀበሌ ይኖር ነበር ።
በመጨረሻም ከሚኖርበት ከገጠሯ መንደር በቃኝ በማለት በሰሜን ጎንደር በሚገኘው ለጎንደሬዎች እነደ ዳግማዊት ኢየሩሳሌም በሚቆጠረው ወደ ዋልድባ ገዳም በገባ በ6 ኛው ወርህ በዛው በዋልድባ ሰቋር በተባለ ገዳም የሕይወት ጉዞው መጨረሻ ሆነ ።
ነፍስ ይማር
ልጅ ሥዩም አብተው ለሰገሌው አንበሳ።
የዋልድባን የቀብር ቦታ በመታረሱ ከማንም በላይ ይሰማኛል የብዙ አርበኞች አፅም ያረፈው በዛው ነው ።

Comments