~~~~ በዘመነ ሕውሓት~~~~~




እኔ የምለው አማራ ተባለው ክልና አማራ የተባለው ሰው አለቀ ልበል ? ወይስ ያፍዝ ያደንዝ አደረጉበት ?


ሚገርም ነው?

በ2/03/2016 በኢሳት ሚዲያ በዜና የቀረበ ነበር እነረዲህ የሚል ።

በአማራው ክልል በምስለኔነት ሕውሓት በአምሳሉ የፈጠራቸው የብአዴን ቅጥረኞች በአማራው ሕዝብ ላይ ሊፈፅሙበት ያቀዱትን እየተወያዩበት እያለ ከውይይቱ ተቀርፆ የወጣው ድምፅ እንዲህ ይላል።


አማራው ወጣቱ የጉልበት ሥራ ሰርቶ ያገኛትን ገንዘብ የጦር መሳሪያ ነው የሚገዛበት ይላል አንዱ ፣

ለምን?

ብሎ የጠየቀ አንድም የለም ።

ለምን ብለው ቢጠይቁ መልሱ ከቅርብ እንደሆን ያውቃሉና የጠየቀ የለም ።

የአማራ ወጣቶች በሀገር ሰርቶ የመኖር በሕውሓት ዘመን የማይታሰብ ነው ሰርቶ የመኖር ሳይሆን አማራ የመኖር መብቱ የተነፈገ እንደሆን ይታወቃል አንድ ቀን የጅምላ ግደያ የዘር ማጥፋት በሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ እንደሚደረግበት ያውቃል ስለዚህ የማይቀረው መከራ እየቀረበ እንደመጣ እየታየ ነው ። 

አማራ በምዕራብ ሀረርጌ፣ በበደኖ ፣በጋራ ሙለታ ፣በአርሲ ፣በጅማ ታርዷል ፣ተፈናቅሏል ፣ 

ከደቡብ ጉራፈርዳ ተገድሏል ተፈናቅሏል፣

አማራ ከምስራቅ ወለጋ አማራ ከጋንቤላ አማራ ከጎጃም ከመተከል ከአሶሳ ፣ አማራ ከጎንደር

 ከወልቃይት ከጠገዴ ከሁመራ ተፈናቅሏል ተገድሏል ይህ ሁሉ በህውሓት አጅረ በሌላ ብሔር 


የሚሳበብበት አንድም ምክንያት የለም ።
እና አሁን ደግሞ አማራ ከጎንደር ከተማ በ25 ኪሎ ሜትር ርቃ ከምትገኘው ትክል ድንጋይ ከተማ 
አማራ ውጣ ተብሎ ከ700 መቶ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው
 የ2008 የትምህርት ዘመን ያለትምህርት ወጣቶቹ ጊዜያቸው በከንቱ ተቃጥሏል ።
አሁን ታዲያ የወያነ ቅጥረኛ በአዴኖች ምን እናድርግ ብለው ነወረ በአማራው ላይ የሚዶልቱት ።
መሳሪያ አምጣ እያልነ እንሰረው ፣

መሳሪያቸውን እንግፈፈው የሚል ተሰብስበው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል ።

አማራ ዋናው የሕውሓት የዘር ማጥፋት አርምጃ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ ብአዴን የአማራውን ሕዝብ 
 እጅና እግሩን አስሮ ወደማጎሪያ ካንፕ አስገብቶ ሊጠብቅ ነው ?
ያለምክንያት ሰውን እንሰረው ሀብቱን እንዝረፈው ይህ እንዴት ነው በቀላሉ የሚታየው ?

Comments