ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ ።

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ ።
=========[[[[[[========>>>
‪#‎ኢሳት‬ ለተጨቆኑ ኢትዮጵያውያን አይንም ጆሮም የመተንፈሻ አካልም ነው
——: Esat
የሀገራችን ፖለቲካ ንቅናቄ ከተጀመረ ከ50 ዐመታት በላይ ቢያስቆጥርም ።
የተገኘው ውጤት ግን ከ50 ዓመት በፊት የነበረውን ተመልሰን በትካዜና በትዝታ እንድንናፍቅ ሁነናል ።
መናፈቅም እንናፍቅ መቸም የሞተ ልጅ አንገተ ረዥም ነው ይባላል ።
★ "ንግባዕኬ ኀበ ጥንተ ነገር እንዲሉ"
ወደ ዋናው ጉዳየ ልመልሳችሁ ።
በዛሬው ዕለት በ29/03/2016
‪#‎በኢሳት‬ ሬዲዮ ጣቢያ "የቀለም ቀንድ" ከምትባል የመፅሔት አዘጋጅ ጋር ያደረገውን ውይይት ተከታትየው ነበር ።
በመጨረሻም የኢሳት ሚዲያ እየሰራ ባለው ቁምነገር እጅግ እረካሁ ።
አወ ! እስካሁን የተጓዝነበትን መንገድ የማያዋጣ የፖለቲካ ውጣ ውረድ ወደተሻለ መንግድ የሚመራ ፀያሄ ፍኖት ( መንገድ ጠራጊ) እንደሆነም ተረዳሁ ተስፋ እንዳለውም ተረዳሁ ።
ስለ ጎንደር ለማውራት በበኩሌ ችግሮችን የሚሰማህን ብትናገር ሰሚም የለህም ከራስህም ሰዎች ጭምር ።
ለምን ጎንደር ጎንደር ሁሌም ጎንደር ትላለህ የሚሉኝ ብዙዎች ናቸው ከኋላቀር ተራ ከሕውሓት የማትለይ ከዘረኛም ተርታ ትመደባለህ ።
ሁሌም የሚያበሳጨው በነዚህ ዓይነት ሰዎች አባባላቸው ነው ። ሕውሓትን አላወቁትም እያዩትም አያውቁት እላለሁ ።
ለኔ ብቻ ነው የሚታየኝ ልበል እልና እራሴን እጠይቃለሁ ።
ሕውሓት በጎንደር እየ ፈፀማቸውና ያለውና ሊሠራቸው ያሰባቸው የሚታየኝ ለኔ ብቻ ነው ? የኔ የዘወትር ጥያቄ ይህ ነው ።
አንዳንዴ ብቻዬን ነው የማወራው ? ብቻየን ነው የምኖረው? የተለየ ዓለም ፣ የተለየ ሀሳብ ፣ ሁሉም ሊቀበለው የማይችል ። አሁን ላይ ምስጋና ለፈጣሪ
ለባለ ጉዳዩ ለጎንደር ሕዝብ ብቻም ሳይሆን የ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በቅርብ የሚከታተለው ጉዳይ ነው በአንድ ቋንቋ መናገር ተጀምሯ ል ። ይህ ነው የሚፈለገው ስለአንድነት ማሰብ በመጀመሪያ በአንድ ቋንቋ መናገር ስንችል ነው ቋንቋ ስል ሀሳብ ለማለት ነው።
የትግራይ ነፃ አውጭ ሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ ኢትዮጵያን ለሩብ ምዕተ ዓመት እንደ ሰም አቅልጦ ፣ እንደብረት ቀጥቅጦ ፣ ኢትዮጵያን እየገዛ ሳለ ገና ትግራይ ነፃ አልወጣችም " TPLF "ስሙን መቀየረም አልፈለገም ስለዚህ ምን ማለት ነው ?
ብለን እራሳችን የጠየቅን ስንቶቻችን ነን?
Shagiz Shagi's photo.
‪#‎ትግራይ‬ ነፃነቷን የምታውጀው መቸ ነው?
ነፃ የምትወጣው መቸ ነው?
ከማንስ ነው ነፃ የምትወጣው?
የመሳሱልትን ጥያቄ መልሱን ለመስጠት የሚከብድ ነገር አይደለም ።
‪#‎አትሩሱት‬ ከቅድመ ደርግ ለ17 ዓመት በጎንደር ብዙ ዐውደ ውጊያዎች ተካሂደዋል ጎንደርነን ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠረው ግን አዲስ አበባን ከያዙ ነው በለይ የወልቃይት ሕዝብ ብቻውን በዛ በኩል ወደጎንደር የሚደረገውን እንቅስቃሴ እየሞቱም እየታፈኑም ገትተውታል በወልቃይት በኩል የነበረው እንቅስቃሴ አቁመው ከወሎ በኩል አቋርጠው ደብብ ጎንደር ላይ ብዙ መስዋዕት ከፍለው ካለፉ በኋላ በወራት ጌዜ አዲስ አበባን ጨብጠዋል ። ሕውሓት ቀለቡን ለመግዛት የሚችለው ከዚሁ ከጎንደር ነበር ።።
ጎንደር ወደሕውሓት እጅ ለመወደቅ ሳትቃረብ ነበር በአጭር ጌዜ አዲስ አበባን የተረከቡት።
የጎንደር ጉዳይ የኢትዮጵያም የሕልውናም ጉዳይ ነው ። አዲስ አበባም ተይዛ ጎንደርን አልተቆጣጠሩም ነበር ።
በሕውሓት መንደር የጎንደር ጉዳይ ቀላል አይደለም ነገሮች ሁሉ ምስጢር ናቸው ለዚህ ድብቅ አጀንዳ የጎንደር ሕዝብ ብቻውን እየከፈለው ያለው ዕዳ የመላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ። ።ለአንዲት ኢትዮጵያ የምናስብ የአንድነት ተሟጋቾች ከሆን ጎንደርን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ማለት ነው ። ለሚገደሉት ጎንደሬዎች መድረስ ካለብን መድረስ ያለብን አሁን ነው ።
‪#‎አትርሱት‬!
ከጎንደር ያሉ ለምና ድንግል መሬቶች ወንዞችና ጅረቶች ታላቁ የሰሜንን ተራሮች ሙሉ በሙሉ የትግራይ ነፃነት የሚታወጀው በወረራ ከተጠቀለሉ በኋላ ነው ።
ለዚህ ሲባል ወደታላቁ የዘር ፍጅት ከመግባታቸው በፊት የወልቃይት የአርማጭሆ ሕዝብ ለቤተ ሙከራ እየተጠቀሙበት ነው የቅማንትም ጉዳይ ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው ።
ሕውሓቶች ወደ አፋር መስፋት ችለዋል ።
ወደቤሻንጉልና ጋንቤላንም እንዲሁ ተቆጣጥረዋል ወስደዋል ታላቋን ክፍለ ሀገር የቀድሞውን ሀረር ሙሉ በሙሉ ሕውሓቶች ከተቆጣጠሩት ዓመታትን አስቆጥሯል ።
የሕውሓት ታላቅ ፈተና ነገር ግን ወሳኝ የሆነው ጎንደር ብቻ ነው ።
ሌሎችን አካባቢ የሚደረጉት ግድያ ሀብት ለመዝረፍ ነው ጎንደር ላይ ግን ዘር ለማጥፋት ነው ።
የሚፈልጉት ሰውን ሳይገሆን ምድሩን ነው ።
ያች ክፉ ቀን ስትደርስ ይህ ለዕርድ የተዘጋጀ ወገኔ የሚሸሽበት እንኳ የለውም በዙሪያ እየከበቡት እያስከበቡት ነው ።
የጎንደር ጉዳይ በምን መልኩ መቋጨት እንዳለበት ብዙ እየሰሩበት ነው ።
ዛሬ በጎንደር በኩል ለሱዳን ተብሎ የሚከለለው መሬት ለታላቋ ትግራይ የሚመለስ የአደራ መሬት ነው ።
—: ከአማራው እጅ ከወጣ በኋላ ወደታላቋ ትግራይ የሚመለስ ነው ። ሱዳኖች የራሳቸውን የነዳጅ ምንጭ የሆነችውን ‪#‎የአብየን‬ ግዛት እንኳ ፈተና ላይ ናቸው ከኢትዮጵያ የራሳቸው ያልነበረን መሬት እሰጥ አገባ የሚገቡበት ምንም ምክንያት የላቸውም ። የሕውሓት ጉዳይ ነው ።
—:ሕውሓቶች እኮ በሰላም ማስከበር ሥም በአብየ ሰራዊት አስቀምጠዋል ይህ ደግሞ ሱዳኖችን ማስፎንደድ የሚችሉበት ደርቲ ፖለቲካ ታላቅ ቁማር ነው በዚህ ቁማርም የደቡብ ሱዳን አዲሷ ሀገር ዋጋ እየከፈለች ነው ።
ከሱዳኖች ጋር ይህም አንዱ የመጫወቻ ጌም ነው ።
ከዚህ ላይ የምንታዘበው ነገር አለ አንድም ፖለቲከኛ እስካሁን ይህን በአደባባይ የሚናገር ብዙም አልሰማም ደንበር ተቆርሶ ለሱዳን ሊሰጥ የሚል ነው ።
ለኔ ይህ የልጆች ጨዋታ የደንቆሮ ጩኸት ነው ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕውሓትን አያውቀውም ።
ሕውሓትን የሚመስል መሰሪ ከዚህ በፊት በዓለም በታሪክም አልበረም ለወፈፊቱም አይኖርም ።
ሕውሓት የተለመደ ዓይነት ተራ አንባ ገነን አይደለም ።
ቅኝ ገዥዎች እኮ በቅኝ የያዙትን ሀገር አይጠሉም ።
ሕውሓት ኢትዮጵያውያንን ብቻ አይደለም የሚጠላው ኢትዮጵያንን ጭምር ነው ።
~~~~ ‪#‎ኢሳትን‬ ይርዱ ~~~

Comments