ሰሜን ጎንደር ትክል #ደንጋይ ከተማ
ከታሪካዊዋ #የጎንደር ከተማ በ25 ኪሎ ሜትር እርቀት የምትገኝ ሲሆን በዚች ከተማ በሕውሓት ትዕዛዝ የአማራ ልጆች ከትምህርት ቤት እንዲባረሩ ስለተደረገ #በ2008 የትምህርት ዘመን #ከ800 በላይ ተማሪዎች ያለትምህርት እንዲቀሩ ተደርገዋል በጭሩ አማራ ከቤንሻንጉል ከጋንቤላ ፣ከጉራ ፈርዳ ተባረረ ሲባል እሩቅ ይመስላችሁ የነበረ እነሆ #ከትክል ድንጋይ ከተማ አማራ አገርህ አይደለም ተብሎ እንዲባረር በሕውሓት ተደረገ ምን እየጠበቀ ነው ?

የሕወሓት የመስፋፋት እቅድ የወለደው የእርስ በእርስ ጦርነት በተክል ድንጋይ ፈንድቷል::
March 27, 2016የሕወሓት የመስፋፋት እቅድ የወለደው የእርስ በእርስ ጦርነት በተክል ድንጋይ ፈንድቷል::
#Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከትላንትና ጠዋት ጀምሮ የሚደርሱ መረጃዎችን ተከትሎ ለማረጋገጥ እንደተቻለው የሕወሓት የመስፋፋት ፖሊሲ እና ታላቋን ትግራይ የመመስረት አላማውን ለማሳካት ሲል የሚሰራቸው እኩይ ተግባራት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈራው የእርስ በእርስ ጦርነት በጎንደር ክፍለሃገር ተክል ድንጋይ መፈንዳቱን ከአከባቢው የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል::ሕወሓት የቅማንት ሕዝብን ለእኩይ ተግባሩ ሊጠቀምበት በማሰብ ከፍተና የሆነ የጦር መሳሪያ እያስገባ ነው የሚሉ የተክል ድንጋይ ነዋሪዎች ይናገራሉ::በአምቡላስ ላይ የደረሰን የፈንጂ አደጋ ተከትሎ ከትላንትና ጀምሮ በሕወሓት የጦር ሰራዊት እና በጎንደር ክፍለሃገር ሕዝብ መካከል ግጭቶች ወደ ተኩስ በመለወጣቸው አከባቢውን የጦር አውድማ አድርገውታል::
በትላንትናው እለት በትክል ድንጋይ በአምቡላንስ ላይ የፈንጂ ጥቃት ደርሶ በአምቡላንሱ ውስጥ የነበሩ ሁለት ሲገደሉ በአንዱ ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሶ የነበረ ሲሆን የአከባቢው ሕዝብ ለአደጋው የሕወሓትን ሰራዊት ተጠያቂ አድርጓል::እንዲሁም ሁለት ታዳጊ ወጣቶች በሕወሓት ጦር መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ::ወደ ተክል ድንጋይ የሚያስገቡ መንገዶች የተዘጉ ሲሆን የሕወሓት ጦር በአከባቢው ውጥረት በመፈጠሩ መሳሪያ ያልታጠቁ ነዋሪዎች ራሳቸውን ከሕወሓት ጦር ለማዳን ወደ ጎረበት ወረዳዎች እየሸሹ ይገኛሉ::መሳሪያ የታጠቁ የተክል ድንጋይ ነዋሪዎች ከወያኔ ጦር ጋር እየተታኮሱ ይገኛሉ:: #ምንሊክሳልሳዊ

Comments
Post a Comment