የአብርሃ ደስታ አስተሳሰብን ከመታሰሩ በፊት እና ከእስራት ወዲህ ያለውን በጥልቅ ያሰብኩበት ።

መጋቢት 23/ 03 /2016
በዛሬው ዕለት ከኢሳት ሬዲዮ የሰማኋቸው ሁለት ነጥቦች ልቤ እየደማ ካለበት ከወልቃይት የሕዝብ መከራ ተጨማሪ ሁኖብኛል ።
1/ የአብርሃ ደስታ አስተሳሰብን ከመታሰሩ በፊት እና ከእስራት ወዲህ ያለውን በጥልቅ ያሰብኩበት ።
2/ በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍል በከፋ ክፍለ ሀገር በትግራይ ተወላጆች ከመያዙም በላይ የዛ አካባቢ ተወላጆች ያመረቱትን ለትግራይ ተወላጀች በ10 ብር እንዲሸጡ ሲገደዱ የትግራይ ሸማቾች ወደውጭ ልከው በዶላር ስንት እንደሚሸጡት ለጊዜው የታወቀ ባይኖርም በሀገር ውስጥ ገቢያ አንድ ኪሎ ቡና በ60 ብር አዲስ አበባ ላይ መሸጥ ይችላሉ ።
ዓመት እስከዓመት የለፋው ገበሬ በ10 ብር እንዲሸጥ ሲደረግ ምንም ያልደከመ ለኪሎ 60 ብር ሽጦ እንዲጠቀም ይደረጋል።
የ21ኛዋ ክ/ ዘመን ኢትዮጵያ እንዲህ ነች ።
ትግራዊ መሆን መታደል አይደለም?
Shagiz Shagi's photo.
R.I.P Ethiopia
ብንል ተሳስተናል?
የህወሓት መፈክር፡ ‘የአማራ የበላይነት ይውደም!’ (በአብርሃ ደስታ)
*************************************************************
"የህወሓት ችግር “የአማራ የበላይነት ይውደም!” የሚል መፈክር ነው። “የአማራ የበላይነት” የሚባለው የህወሓት በሽታ እስካሁን ፈውስ አላገኘም። በመርህ ደረጃ ህዝብን ዒላማ አድርጎ ህዝብን ለመታገል መነሳት ስህተት ነው ብያለሁ። በፖለቲካ ህዝብን ዒላማ አይደረግም። ምክንያቱም የፖለቲካ ዓላማ ህዝብን ማገልገል እንጂ ህዝብን መጨቆን አይደለም። ስለዚህ ህዝብን የመበደል ዓላማ መያዝም መተግበርም የህሊና ወንጀል ነው። ህወሓቶች ይህን በሽታ (“የአማራ የበላይነት” መፈክር) አልተዋቸውም። አሁንም “ፀረ አማራ” እንቅስቃሴዎች አሉ። የህወሓት የአሁኑ ስትራተጂ “እኛ ከስልጣን የምንወርድ ከሆነ ከአማራ ጋር አብረን አንቀጥልም” የሚል ገንጣይ አስተሳሰብ እያራመዱ ይገኛሉ። “እኔ ከሌለሁ ሠርዶ አይብቀል …” ዓይነት ስትራተጂ መሆኑ ነው። በጣም የሚገርመው ነገር ፀረ ብአዴንም መነሳታቸው ነው። ለነሱ ከስልጣን ከሚወርዱ ኢትዮጵያ ብትበታተንና ትግራይን አስገንጥለው ትግራይን እየጨቆኑ ቢገዙ ይመርጣሉ።
ግን ይህን “አማራ” የሚባል ህዝብ መቼ ይሆን የበላይነት ይዞ ሌሎች ህዝቦችን የበደለው? አንድን ህዝብ እንዴት ሌላውን ህዝብ ይበድላል? ህዝብ ህዝብን ሊበድል አይችልም። ምክንያቱም አንድን ህዝብ ሌላውን ህዝብ መበደል ከጀመረ (ከቻለ) ህዝብ መሆኑ ቀርቶ ገዢ መደብ (elite) ሁነዋል ማለት ነው። ገዢ መደብ ከሆነ ደግሞ ህዝብ አይደለም። ገዢ መደብ ስርዓት ነው። ህዝብና ስርዓት ደግሞ ይለያያሉ።
ምናልባት የህዝብ የበላይነት አለ የምንለው ህዝብን የሚያስተዳደር (የሚገዛ) ስርዓት ከህዝቡ የወጣ ሲሆን ይሆን? ይህም አሳማኝ አይደለም። ምክንያቱም ገዢ ሁሌ ከህዝቡ ነው የሚወጣው (የቅኝ ግዛት ካልሆነ በስተቀየር)፤ ገዢ ከህዝቡ እንጂ ከማርስ አይመጣም። የኢትዮጵያ መሪ ከኢትዮጵያ ህዝብ ይወጣል። በኢትዮጵያ ብዙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሉ። ስርዓቱ ከሁሉም ህዝቦች ሰዎች ይኖሩታል። መሪ ግን አንድ ነው የሚሆነው። ያ አንድ ሰው (መሪው) ከአንድ ብሄር ሊሆን ይችላል። ያ አንድ ሰው ስልጣኑ ተጠቅሞ ሌሎች ህዝቦችን ሊበደል (ወይ ሊጠቅም) ይችላል። ሰውየው የፈጠረው ስርዓት ለህዝቡ ቢጎዳም ቢጠምም ከስርዓቱ ይገናኛል እንጂ መሪው ከመጣበት ብሄር ጋር አይገናኝም። ስለዚህ ገዢዎች የሚወክሉት የፈጠሩትን ስርዓት እንጂ የመጡበትን ብሄር አይደለም።
የደርግ ስርዓት ሲበድለን፣ “አማራ በድሎናል” ይሉናል። የኃይለስላሴ ስርዓት ሲበድለን “አማራ በድሎናል” ይሉናል። የምኒሊክ ስርዓት ሲበድለን “አማራ በድሎናል” አሉን። የህወሓት ስርዓት ሲበድለንስ ማን በደለን ሊሉን ነው? የትግራይ ህዝብ? አይሆንም። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ የትግራይን ህዝብ ይበድላል? አንድን ህዝብ ራሱን ይበድላል? በደል ሁሉ ወደ አማራ ህዝብ ለምን? ስርዓትና ህዝብ ማገናኘት የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል።
ግን እስቲ ይሁን፤ መሪዎች የመጡበትን ብሄር ይወክላሉ እንበል (ስህተት ቢሆንም)። እነሱ (መሪዎቹ) ሲበድሉ የመጡበት ብሄር በበዳይነት ተፈርጆ እንደ ጠላት ይቆጠር እንበል። የአማራ ህዝብ መቼ ይሆን በመሪዎቹ አድርጎ ሌሎች ህዝቦችን የገዛ (የበደለ)? ያለፉ ጨቋኝ ስርዓቶች አማራ ነበሩ ያለው ማነው? አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ አይደለም። እስቲ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መሪዎች እንመልከት።
ብዙ ግዜ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው ከአፄ ቴድሮስ ነው (ወይም ከዚሁ እንጀምር! ምክንያቱም ከአፄ ቴድሮስ በፊት ኢትዮጵያ በመሳፍንቶች ነበር የምትተዳደረው። በዘመነ መሳፍንት መሳፍንቶች የራሳቸውን ህዝብ (ብሄር) ይገዙና ይበድሉ ነበር)። “አማራ” ተብሎ ከተሰየመው አከባቢ የሚወለድ ገዢ ቴድሮስ ነው። አፄ ቴድሮስ ኢትዮጵያ አንድ ለማድረግ በዛን ግዜ የነበሩ መሳፍንቶች ተዋጉ። አፄ ቴድሮስ ዉግያው የጀመሩት በአማራ መሳፍንቶች (የጎጃም፣ ወሎና ጎንደር) ነበር። ቴድሮስ “ከአማራ ስለመጣሁ፣ አማራ ስለምወክል፣ የአማራ መሳፍንቶች ማጥፋት የለብኝም” አላሉም። (ህወሓት ለትግራይ መሳፍንቶች እንዳደረገው ሁሉ)። ስለዚህ አፄ ቴድሮስ አማራን ወክለው ሌላው ኢትዮጵያዊ አልበደሉም (ከበደሉም ለሁሉም ነው)። ስለዚህ “በአማራ ህዝብ ተገዛን” የሚለው ክስ “በአፄ ቴድሮስ ተገዛን” የሚል እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ።
የአማራ ተወላጅ የሆነ የኢትዮጵያ ገዢ ቴድሮስ ብቻ ነው ብዬ አስባለሁ (ጉዳዩ ለታሪክ ተመራማሪዎች ልተወው እንዳልሳሳት፤ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ)። ዮሃንስ አማራ አልነበረም፣ ምኒሊክ አማራ አልነበረም፣ ኃይለስላሴ አማራ አልነበረም፣ መንግስቱ አማራ አልነበረም፣ መለስ አማራ አልነበረም፣ ኃይለማርያም አማራ አይደለም። ማነው አማራ?
ምናልባት “የአማራ ገዢዎች” የምንለው ግለሰቦቹ (ንጉሶቹና መሪዎቹ) ሳይሆን ስርዓቱ ነው ካልን ያው ስርዓቱማ ከሁሉም ህዝቦች ተወካዮች አሉበት። አማራ ለብቻው ገዥ ነበር ማለት አንችልም። ምናልባት ገዢዎቹ አማርኛ ስለሚናገሩ ነው ካልን ደግሞ አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ አይደለም። አቶ መለስም አማርኛ ይናገር ነበር። አፄ ዮሃንስም አማርኛ ይናገሩ ነበር (አማርኛ የኢትዮጵያ ኦፊሽየላዊ የስራ ቋንቋ እንዲሆን የወሰኑት አፄ ዮሃንስ ናቸው የሚል መረጃ አለኝ፤ ‘መረጃ’ እንጂ ‘ማስረጃ’ አላልኩም)።
የአማራ ህዝብ እንደ ማንኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በኢትዮጵያ ገዢዎች ሲሰቃይ የነበረ ነው። ባልበላበት በልተሃል፣ ባልገዛበት ገዝተሃል ሲባል ይገርማል.። ያለፉ ገዢዎች አማርኛ ስለሚናገሩ ከአማራ ህዝብ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም። ህዝብ ሌላ ገዢ ሌላ።"

Comments