Great thanks to ESAT.

 Great thanks to ESAT.
~~~~~~~~~~~~~~
ለኢሳት ሚዲያ ከፍ ያለ ምስጋ አቀርባለሁ ።
ኢሳት ባይኖር ኖሮ ይህኔ በወልቃይት በጠገዴ ሕፃናት አዕሩግ ቆነጃጅት እና ጎረምሶች ናቸው ሳይባሉ አማራ ነን ያሉ በሙሉ በጅምላ ይገደሉ ነበር በጅምላ ይቀበሩ ነበር ።
የሚፈለገው የአማራን ሕዝብ መቀነስ ብሎም ለማጥፋት ነው ዓላማው ።
ነገር ግን እድሜ ለኢሳት ሚዲያ የወጣት ሊላይ ብርሃኔ ታፍኖ መሰወር በይፋ መውጣቱን ተከትሎ በኢሳት ሚዲያ ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው በመደረጉ ይህ ያሳለፍነው የሩዋንዳውን ዓይነት የዘር ማጥፋት ዳንሻ ላይ ይካሄድ ነበረ ።
በዚህ ላይ መረሳት የሌለበት የሕውሓት ጆከሮች እንደ እስስት ቀለማቸውን እየቀየሩ እንደአሜባ ራሳቸውን አያባዙ በኢሳት ሚዲያና በትጥቅ ትግል ነው ወያኔን መውደቅ አለበት ብለው በሚያምኑት ላይ ከፍተኛ የማጥላላትና ባይኮት በመጥራት ላይ ነበር የከረሙት ።
በኦሮሞው ሕዝብ አመፅ ወቅት ቅስማቸው ተሰብሮ ጫና ስለ ተፈጠረባቸው ድምፃቸው አጥፍተው የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ደግሞ የወልቃይቱ ጉዳይ እኛ ነው እንመራው እያሉን ይገኛሉ ።
እኔ በቀላሉ አውቃቸዋለሁ ስማቸውን ቢቀይሩም እስታይላቸውን አይቀየሩም ።
ሁላችሁ አማራ ነን የምትሉ የሕውሓት ጆከሮችን ላይ በስመ አማራ እነ ሴብ አደና እነ ዘ ፀአት አክሱም አማራ ነን እያሉ ከመካከላችን አሉ ምን ችግር አለው ከኛ በላይ ለአማረኛ ረቂቅ የሚያወጡ እነሱ ናቸው ።
ልብ በሉ አንድን ነገር በመደጋገም እንዲሰለች የሚያደርጉት እነሱው ናቸው
። አሁን ላይ ስለ ፕሮፊሰር አሥራት ወ/ጌስ ማንም አያነሳም አያወሳም ይህ የሆነበት ምክንያት በፕ/ ሩ ሥም ከእርሳቸው ዓላማ ጋር የማይሄድ ተራ አሉባልታ በከፍተኛ ፈረጃ ተካሂዶባቸዋል በነዚህ የሕውሓት ጆከሮች ሰው ሰራሽ አማራዎች ።
በታዋቂ ሰዎቻችን ላይ በግሩ ሲሳደቡም በአማራው ሥም በበለይ ዘለቀ በአፄ ቴዎድሮስ ። በመሳሰሉት እየተጠቀሙ ነው ።

እኛ እየሞትን እየተፈናቀልን እየተሰደድን እየታሰርን ጀግናው አማራ ወዘተ ይሉሀል በአማራው ሁሌም ጉራ ነገር የሚፅፉት እነሱው ናቸው ። አማራው ዛሬ የወሎ ሥም ይቀየር የሚልበት ዘመን ነው አማራው ከጎንደር መሬት ከጎጃም ለምለሙ መሬቱን እየተቀማ የአማራ ደንበር እስከባሌ ነው ይሉና ካርታም ይሰራሉ ኦነገረ ሻዕቪያ የሚሉ መሙዚቃዎችም ያበዛሉ ልክ እንደፈጣሪያቸው ሕውሓት ሚዲያ ETV
አማራ እየሞተ እነሱ በአማራው ሥም በምፀት ይሳለቃሉ ።
ለዚህ ሁሉ ሕዝባችንን ብሶቱ ለወገኑ ለማሰማት በጨለማዋ ከዛ ከገጠሯ ድረስ ኢሳት ዘልቆ በመግባት የእናቶችን ድምፅ ከቤታችን ደረስ ይዞልን ይደርሳል ።
አወ ከዛ ከበረሃው ከአርማጭሆ ነው አሎ !!! አሎ !!!
አሎ የእናት ድምፅ ይሰማል ቀጥሎም አሎ ! አሎ •••••አሎ የምደውለው ከወልቃይት ነው!
አሁንም ሌላኛዋ እናት ባለቤቷን እንደከብት በሌሊት የተሰረቀባት።
አሎ !! ••••• አሎ ! ከጠገዴ ነው
አሎ !!! ••••• ከዳንሻ ነው !
አሎ ! ••••• ከሰሮቋ ነው የእናቶች ድምፅ ይሰማል የወላድ መካኖቹ ።

Comments