የልጅነት ዘመን ሀሁ ት/ ቤት ከየኔታው ወንበር ።

ከልጅነት ትውስታየ ተመሳሳይ ትረካ 


የልጅነት ዘመን ሀሁ ት/ ቤት ከየኔታው ወንበር ።
አንድ በእድሜ ከኔ ጠና ያለ የትግራይ ተወላጅ ከመንፈሳዊነት ወደዘመናዊነት የሚያደላው ዘርዓዳዊትን እንዳስታውሰው አደረገኝ ።
አስተማሪያችን የትውልድ ቦታቸው ከአማሴን ይሁን እንጅ ወገራ ለኒህ መምህር ሁለንትናቸው ነች ።ዘምድናም ቋንቋ ነው ፣ ዘርና እና ዝምድና ትርጉም ቦታ የለውም፣ ለየኔታ ስሜት ሰጫቸው አልነበረም ሀገራቸው ኢትዮጵያ ወገናቸውም ወገራ እና የወገራ ሕዝብ ነው ።
እኒያ የቀለም ቀንድ አስተማሪ ጉባይ ከፍተው አቋቋም ፣ዝማሬ መዋስዕት ከማስተማራቸውም በላይ የማስመስከሪያም ነበሩ ፣ እኒህ አባት በዚች በዓት ከጠላት ወረራም በፊት የኖሩበት ምድር አካባቢም ነው ።
የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ትግርኛ ቢሆንም ከመስማት ባሻገር ለመናገር እነደሚከብዳቸው አውቅ ነበር ።
ወደጓደኛየ ዘርዓዳዊት እንመለስ ።
ዘርዓ ዳዊት በዚህ ጉባኤ አቋቋም ለመቀፀል ወደወገራ ከትግራይ የመጣው ከአብዮት በኋላ ነው ዘመኑም የእድገት በሕብረት ዘመቻ ወቅት ነው
ኢህአፓ ወደሀገር ቤት ካድሬወቻቸውን ያሰማሩበት ወቅት ነው ።
የኢህአፓ ካድሬዎች በዚህ የአቋቋም ተማሪዎችና የደብሩን ዲያቆናትም በድብቅ እየለዩ ያወያዩ ነበር እኔም በጓደኞቸ ተገፍቸ ወደዛው ውይይት እታደም ነበር እነዛ የኢህአፓ ካድሬዎች በተዘጋች ጎጆ ውስጥ የማኦ ሴቱንግን መፅሀፍ ነበር የሚተርኩልን ።
ብዙም ሳይቆይ በእድሜ ከጓደኞች ያነሰ ቢሆንም በጓደኞቸ መካከል ተፅዕኖ መፍጠር የምችል እንደነበር አውቃለሁ እናም የተለያዩ ነጥብ ላይ ጥያቄም አነሳ ነበር ።
ፔዛንቱ ለትጥቅ ትግል ለአባልነትም አያስፈልግም በአጋርነት ካልሆነ የሚለውን የኢህአፓ አቋም እንደሆነ ሲነግሩን ። እንዴት? ለምን? ብየ ጥያቄ አነሳ ነበር ፣
ኢህአፓ ገበሬውን ሊጠቀምበት ብቻ የፈለገው እንደሆነ ተረዳሁ ።
አስታውስ አለሁ አንድ የአጎቴ ልጅ ለብቻ እኔን ማነጋገር ፈለገና ወደቤቴ ሲሸኘኝ በምሽት ጨረቃ ብዙ መንገድ ላይ ቁመን አወራን ዳግም ወደውይይቱ እንደማልመጣ ስነግረው በጣም ነበር የደነገጠው ትሞታለህ ነበር ያለኝ ።
ያ ጓደኛችን የትግራይ ተወላጅ ዘርዓ ዳዊት
በዚህው አካባቢ የኢህአፓን ፖለቲካ ከነዛ ካድሬዎች ባልተናነስ ያመነበት ነበር ሆኖም ግን በጓደኝነታች ምንም እንከን አልተፈጠረም ነበር ።

እንዲያውም ከኔ ጋር እጅግ የጠበቀ ነበር ።
ይህ ጓደኛዬ ዘርዓዳዊት በስጋ ከሚወለደው ወንድሙ አስበልጦ ለኔ ፍቅርና እምነት ነበረው ቢሞት አብሬው የምሞት ይመስለውም ነበር ለኔም እንዲሁ ተመሳሳይ ስሜት ነበረኝ ።
ከዘርዓ ዳዊት ጋር ከገጠር ወደከተማ አብረን በምንጓዝበት ወቅት ለምን ሽጉጥ እንደሚይዝ ባላውቅም ሽጉጥ አይለየውም ነበር ፣ ሽጉጡን አንተ ያዝልኝ ይለኝ ነበር ወደከተማ ሽጉጡን የማስገባለት እኔው ነበርኩ ይህ አካሄዱ ከኢህአፓ ክስረት በኋላም የቀጠለ ነበር ።
በአንድ ወቅት የሆነ ጭቅጭቅ ና ሙግት ነበረው ።
በአቋቋም ተማሪዎች ከትግራይ በመጡና ሁለት የሰሞነኛ ተማሪዎች የጎንደር ልጆች ይደበደባሉ ሕፃናት ናቸው የጥሉ መንስኤ የቀፋ ወይም የልመና መንደሮችን ወሰን ተጋፋችሁ የሚል ነበረ።እነዛ ልጆች ጥርስ ወልቆ ስለነበር ።
ጉዳዩ ለፍርድ ቤት ሲቀርብ አስተማሪያች እኒያ የቀለም ቀንድ ደብዳቢ ተማሪ የርሳቸው በመሆናቸው በኃላፊነት ሲከሰሱ ሰውየው ወጥተው ወርደው መከራከር ስለማይችሉ ይህ ዘመናዊው የመንፈሳዊ ተማሪ ዘርዓዳዊት ተወክሎ ይከራክር ነበር ።
በዚህ የተነሳ በግልም ከልጆቹ የሥጋ ዘመዶቻቸው ዛቻ ውስጥም ስለነበር ሁሌም አብሬው የምወጣና የምወርድ ጓዳኛው ነበርኩ በመጨረሻም ከገጠር ወደከተማ በ1997 ዓ/ ም የገባነው በአንድ ላይ ነበር ፣ እሱ ወደ ጋራጅ ሥራ ሲጀምር እኔ መደበኛ ትምህርት ቤት ገብቸ ቀጠልኩ በዚህ የጎንደር ከተማ ቆይታየ የማይረሳ የቅርብ ጓደኛዬም ነበር ከሁሉም በላይ ሳይክል ሰጥቶኝ በሱ በሰጠኝ ሳይክል ተለማምጀ እንኳንስ ለራሴ ለጓደኛም እየሰጠሁ እጠቀም ነበር ። በመጨረሻ ከዘርዓ ዳዊት ጋር ለአንደፀና ለመጨረሻም የተለሁት በዚሁ በጎንደር ከተማ ነበር ዓመተ ምህረቱን አላስታውስም ።
የጋራዥ ልምዱን ከምህፁን ጋራዥ አፅፎ ታይፕ ሲያስመታ አብሬው ነበር ከሀገር እንደሚወጣ ወደአረብ ሀገር እንደሚሄድ ነግሮኝ ነበር ።
ከብዙ ዓመት በኋላ ነበር በሱዳ እንደሚኖር የሰማሁት እኔም ወደሱዳን ለመሄድ አስቤ ደብዳቤ ፅፌለት ፣ የፃፍኩለት ደብዳቤም እንደደረሰው እና መልስ ባይፅፍልኝም ደባዳቤ ለሰጠው ሰው አያስፈለግም አትምጣ ብለህ ንገረው እንዳለ ሰማሁ እና ባዕድ እንደሆን የተረዳሁበትም ወቅት ነበር ።

Comments