በኛ ፈረቃ ሀገር ስትፈርስ ዝምታን መምረጥ የለብንም ።

 
የሀገራችን ሁኔታ የሚያስዝነው ጥቂቶች መራራው ፅዋ እንዲህ በወጣትነት እድሜ ሲጎነጩት ከኛ በላይ ለሀሰሰር ነው የሚሉት ደረጃ አውጭዎች ፀጉር ሰንጣቂዎች እነ የጋን መብራቶች መስለውና ተመሳስለው በግል ጥቅም ብቻ ተደልለው የሁላችንም ሀገር በመቃብር አፋፍላይ ቁማ ዜጎች ላያቸው ላይ ቤት ፈርሶ ሀገረ ኢትዮጵያ ሳይኖራት በነፃ አስተምራቸው ባገኙት አጋጣሚ ከሀገር እየከዱ ወጥተው የፈረንጅ አገልጋይ ሁነው ባፈሯት ቲኒሽ ሳንቲም ተመልሰው ለዚህ ፀረ ሀገር ዘረኛ ና ጠባብ ሀገር በቀል ወራሪ የቅኝ ገዥ ቀጥተኛ ተሳታፊ አቃፊ ና ደጋፊ በመሆን የድሆችን መኖሪያ አስፈርሰው ባለፎቅ ባለመሬት ባለሀብት ሁነው እናያለን የተቀሩት ደግሞ ስለሀገር ማውራት መሰብሰብ መወያየት እርማቸው አድርገው ዝምተሰን መርጠው ሲቀመጡ አብዛኛዎቹ ምሁር ነን ባዮች ከኢንጅነርነት ወደ ፓስተርነት ተቀይረው ጌታን ተቀበልን አገኘነው እያሉን በሀገር ቤት ለሚደርሰው በደል ጭቆና ስታነሳባቸው አምጡ ዱላዬን የሚሉት ከሕውሓት መንግሥት ለሀሳር ነው ይሉሀል እድገቱ ልማቱ ይሉሀል ።
ይህን ትውልድ እከሳለሁ ።

ሀገርን ለነ ኢየሩስ ብቻ አይደለችም፣ የነእስክንድር ብቻም አይደለም ።
የት ገቡ የአራዳ ልጆች በ25 ቱ የሕውሓት የስልጣን ዘመን ቁሞ የሚገረፍ ።
ከዚ አንፃር የሀገሬ ገበሬ ክንዴን ሳልንተራስ እያሉ ሶስት አራቱን እየጣሉ የወደቁት አውቃለሁ።
ኘገን ያራዳ ልጅ እነ ድንጋይ ኳሱ ፣
ከምኔው ተጩሆ ከምኔው ደረሱ ፣
 
አንዱን ቤት አፍራሽ ደንቆሮ የሕውሓት ካድሪ ላይ ነበር አራዳነትን መግለፅ እንደናቱ እንባውን አብሶ መቀመጥ የት የተወረሰ ነው ?
እምብኝ አሁንም እምብኝ ።

Comments